የስብሰባ ጥሪ
የኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር 6ኛ ድንገተኛና 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
ቀደም ሲል ህዳር 17 በወጡት የሪፖርተርና የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታህሳስ 18 ቀን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ የወጣው ማስታወቂያ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተቀይሯል፡፡በመሆኑም የኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር 6ኛድንገተኛና 12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በግሎባል ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
1. የ6ኛ ድንገተኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1.1. የማህሩን መመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል፡፡
2. የ12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
2.2. የማህበሩን የዳሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፓርት ማድመጥ፤
2.3. የማህበሩን የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፓርት ማድመጥ፤
2.4. በቀረቡት ሪፓርቶች ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
2.5. ለመጪው ዘመን የውጪ ኦዲተር መምረጥና ክፍያውን መወሰን፤
2.6. የኤደን ቢዝነስ አ/ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ የአሠራር ደንብ ማፅደቅ
2.7. አዲስ የቦርድ አባላት ምርጫ ማካሔድ ፣
ማሳሰቢያ
1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባኤው እለት ቢያንስ ከሶስት የሥራ ቀናት በፊት ማህበሩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ ሳርቤት አካባቢ በሚገኘው ኢገስት ሕንፃ የማህበሩ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ድረስ በአካል በመቅረብና በመፈረም በወኪሎቻቸው አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተረጋገጠ የውልክና ማስረጃ የያዘ ተወካይ የማሰረጃውን ዋናና ቅጂ ይዞ በመቅረብ በስብሰባው መሳተፍ ይችላል፡፡
2. ሁሉም ባለአክሲዮኖች ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ እና የባለአክሲዮን መለያ ቁጥር ይዘው በመምጣት በስብሰባው እንዲገኙ በትህትና እንጠይቃለን፡፡
3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ሥም ዝርዝር ከታህሣሥ 10 ቀን ጀምሮ በዋናው መሥሪያ ቤት ማስታወቂያ ሠሌዳና በድርጀቱ ድረ-ገፅ www.edenbusiness-sc.com/news ስለሚለጠፍ መመልከት ይቻላል፡፡
የኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
የዳሬክተሮች ቦርድ